የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ እሴት በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሰተላለፍ ይገባል – ዶ/ር ሂሩት ካሳው
አዲስ አበባ፣መስከረም 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ከአባቶቻችን የተረከብነውን የመስቀል በዓልም ሃይማኖታዊ እሴቱን በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሰተላለፍ እንደሚገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሰዉ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት በአዲስ አበባ መሰቀል አደባባይ ባድረጉት ንግግር፥ በዓሉን ስናከበር የተሰጠንን ሃላፊነት በብቃት በመወጣት ሰላምና ፍቅርን በማስተማር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የምንወዳትን ታላቅ ሃገር ልዕልናዋን አስጠብቆ ለማቆየት በትጋት መስራት ይገባናል ሲሉም ሚኒስተሯ ተናግረዋል፡፡
በአዲሱ ዓመት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሃላፊነታቸውን በብቃት በመወጣት፣ ፍቅርን በመስበክ እና ጥላቻን በማሰወገድ በሁሉም ዘርፍ ሊንቀሳቀሱ አንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከአባቶቻችን የተረከብነውን የመስቀል በዓልም ሃይማኖታዊ እሴቱን በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሰተላለፍ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በዓሉ በሰላም አንዲከበር ላደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅረበዋል ፡፡
በሚኪያስ አየለ