የወረኢሉ ከተማ ነዋሪዎች 22 ጣቃ አልባሳት ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወረኢሉ ከተማ ነዋሪዎች ከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ አልባሳትን ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።
የከተማው ነዋሪወች እና የንግዱ ማህበረሰብ በእያንዳንዳቸው በማሠባሠብ 22 ጣቃ አልባሳትን ነው ለደቡበ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ያስረከቡት።
ድጋፋ ለአራስ ህጻናት ለታዳጊወችና ለእናቶች የሚሆኑ አልባሳት በብዛት ያሉት ሲሆን፣ የአዋቂወች እና የሌሊት ልብሶችም ተካተውበታል።
የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዋለ በቀለ ፥ የከተማችን ህዝብ በወገኖቹ መፈናቀል አዝኗል እንደዛሬው ሁሉ ነገም በሚያስፈልገው ሁሉ ከእነሱ ጋር እንቆማለን ብለዋል።
የከተማው ህዝብ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተወካይ አቶ አደም ሰይድ በበኩላቸው ወገኖቻችን በችግር ውስጥ ሆነው እኛ በሞቀ ቤት ደልቶን ልንኖር አንሻም ሁለት ያለው አንዱን በመለገስ ድጋፋችን ቀጣይ ይሆናል ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሣይ ማሩ የከተማ አስተዳደሩ ህዝብ ስላደረገው ድጋፍ አመሥግነዋል።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!