አቶ ደመቀ መኮንን ከተመድ ዋና ጸሐፊ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተመድ ዋና ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኒው ዮርክ ተገናኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ወገኖች ስለኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ስላለው ሁኔታ አንስተው ተወያይተዋል።
በኢትዮጵያ ሰላም ማምጣት በሚቻልበትና አሸባሪው ህወሓት በፈጠረው ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!