አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ዛሬ ይመሰረታል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ በሚያካሄደው ጉባኤ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይመሰረታል።
በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለጨፌ ኦሮሚያ የተመረጡ አባላት በመጀመሪያ ጉባኤያቸው ክልሉን ለአምስት ዓመታት የሚመራ አካል ይደራጃል፡፡
አዲሱ ጨፌ በመጀመሪያ ጉባኤው አዲሱን የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት እንደሚሰይምም ይጠበቃል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ይሰየማሉ፤ የክልሉ የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤም እንደሚዋቀር የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!