Fana: At a Speed of Life!

ከሰሜን ወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች በ12 ሚሊየን ብር የተገዙ ቁሳቁሶች ተሰጡ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ነዋሪነታቸው በውጭ አገር የሆነ ኢትዮጵያውያን ስብስብ የሆነና አማራ ኢመርጀንሲ ፈንድ የተባለ ድርጅት ከሰሜን ወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች በ12 ሚሊየን ብር የተገዙ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበርክተዋል።

ድጋፉን የላኩት አሜሪካ፣አውሮፓ፣ካናዳና አውስትራሊያ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆች ናቸው ።

የድጋፉ ዓይነት በተለይ ነፍሰጡሮችን ፣ የሚያጠቡ እናቶችንና ከሁለት ዓመት በታች የሆናቸውን ህፃናት ማዕከል ያደረገጉና በልዩ ትዕዛዝ የተመረቱ አልሚ ምግቦች መካተታቸውን ከድጋፉ ስርጭት አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ምስጋናው ቸርነት ተናግረዋል።

እድሜአቸው የገፋ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችም በድጋፉ ተካተዋል።

ከድጋፎቹ መካከል ዱቄት ፣ ፍራሽ፣ ብርድልብስ፣ የህፃናት አልባሳት ይገኙበታል።

በተመሳሳይ በጎንደር ለተፈናቀሉ ወገኖች መሠል ድጋፍ ይደረጋል፤ ይሄ የመጀመሪያ ዙር ነው ብለዋል አስተባባሪው።

በዘመቻው ለተጎዱ የሰራዊት አባላት የሚውል ድጋፍም ተዘጋጅቷል ያሉት አቶ ምስጋናው፥ ዜጎችን መልሰው እስከሚቋቋሙ ድረስ ድጋፉን እንቀጥላለን ብለዋል።

በእሌኒ ተሰማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.