Fana: At a Speed of Life!

የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች መሸለማቸውን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ውድድሩ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ አካባቢ ፈንድ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ልማት ፈንድእና ከተባበሩት መንግስታት ካፒታል ልማት ፈንድጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
አሸናፊ ለሆኑ 19 የሦስተኛ ዙር ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዳቸው 8 ሺህ ዶላር ወይም 348 ሺህ 721 ብር ፣ ለ9 የ4ኛ ዙር ውድድር አሸናፊዎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 33 ሺህ 333 ዶላር ወይም 1 ሚሊየን 453 ሺህ 8 ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በሳካይ ላይት ሆቴል የተካሄደውን የሽልማት መርሐ ግብር በንግግር የከፈቱት በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍሬሕይወት ወልደ ሐና፥ ሽልማቱ ዘላቂ የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጅዎችን ለማስፋፋት በ2016 ይፋ በሆነውና የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ አካባቢ ፈንድ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ልማት ፈንድ እና ከተባበሩት መንግስታት ካፒታል ልማት ፈንድ ጋር በጋራ በመሆን የሚተገብረው ፕሮጀክት አካል መሆኑን ጠቁመዋል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዓለማ በገጠር የሚኖረው የሕብረተሰብ ክፍል ለቤት ውስጥና ለሌሎች የምርት ሂደቶች ታዳሽ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀም ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም የዛላቂ የልማት ግቦች ግብ 7 እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ የኢነርጂ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ማሳካት መቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህ ታዳሽ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ላይ የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ኢንተርፕራይዞችና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ገልጸው፥ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሽልማትና ለሥራቸውም እውቅና የሚሰጥበት መሆኑን በመጠቆም በውድድሩ አሻናፊ ለሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ዘላቂ የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፊያ ፕሮጀክት ታዳሽ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋትና በገጠር የሚኖረው የሕብረተሰብ ክፍል እንዲጠቀም በማበረታታች የካርቦንዳይኦክሳይድን ልቀትን ለመቀነስና ኢነርጂን ለመቆጠብ በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በልማት አጋሮች ትብብር በመተግበር ላይ ያለ ፕሮጀክት መሆኑንከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
22
Engagements
Boost Post
21
1 Share
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.