Fana: At a Speed of Life!

ለ33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እንግዶች በሚያልፉበት ወቅት ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ጥር 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለ33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እንግዶች በሚያልፉበት ወቅት ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ – ወሎ ሰፈር – ኦሎምፒያ መስቀል አደባባይ – ብሄራዊ ቤተመንግስት-ጊቢ ገብርኤል መታጠፊያ – ሸራተን አዲስ – አራት ኪሎ፣

• ከቦሌ አየር መንገድ – በሚሊኒየም አዳራሽ – ወሎ ሰፈር – ኦሎምፒያ – ጋዜቦ -በአዲሱ መንገድ – ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ – ቡልጋሪያ ማዞሪያ – አፍሪካ ህብረት፣

•ከፓርላማ መብራት – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – አደባባይ – ብሄራዊ ቤተመንግስት – በፍል ውሃ – ብሄራዊ ትያትር – ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት፣

• ከአራት ኪሎ – ሸራተን ሆቴል – ሀራምቤ ሆቴል – ብሄራዊ ትያትር መብራት ወይም አንድነት መብራት – ሰንጋ ተራ – ዋቢ ሸበሌ – ሜክሲኮ አደባባይ – ትምባሆ ሞኖፖል – አፍሪካ ህብረት፣

• ከቦሌ አየር መንገድ- በሚሊኒየም አዳራሽ – ወሎ ሰፈር- ኦሎምፒያ – መስቀል አደባባይ – ብሄራዊ ቤተ-መንግስት – ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ – አራት ኪሎ እንግዶች በሚያልፉበት ወቅት ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ናቸው።

ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱት መንገዶች ዝግ በሚሆኑበት ሰዓት ህብረተሰቡ የሚከተሉትን ተለዋጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች፦

• በኮካ ኮላ ድልድይ – አብነት ተክለኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ
ለቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች

• በአትላስ -ዘሪሁን ህንጻ – ሲግናል

• በቀለበት መንገድ – መገናኛ – ዲያስፖራ አደባባይ – እንግሊዝ ኤምባሲ

• በቀለበት መንገድ – መገናኛ – አድዋ ጎዳና – አዋሬ አራት ኪሎ ያሉትን መንገዶች በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.