Fana: At a Speed of Life!

ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለአገር መከላከያ ሠራዊት 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለአገር መከላከያ ሠራዊት ከድርጅቱ አመራርና ሠራተኞች የወር ደመወዝ የተዋጣውን አራት ነጥብ ሦስት ሚሊየን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ አስረክቧል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀይለማሪያም፥ ከድርጅቱ የተደረገውን ድጋፍ ለመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል አስረስ አያሌው ንው ያስረከቡት።
ድርጅቱ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት “ሺህ ዓመት ተፈትና ያሸነፈች አገር – ኢትዮጵያ” በሚል በነጋሪ መጽሄቱ 18ኛ ልዩ እትም ያዘጋጀውን አንድ ሺህ ቅጂ ለአገር መከላከያ ሠራዊት በስጦታ አበርክቷል።
በኢዜአ የነጋሪ መጽሄት ምክትል ዋና አዘጋጅ አቶ ፍፁምእሸት ሽመልስ የመጽሄት ስጦታውን ለመከላከያ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል አስረስ አያሌው አስረክበዋል።
የመከላከያ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል አስረስ አያሌው አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች መሰረተ ልማት በማውደም፣ ሕዝብ በማፈናቀል፣ ዘረፋና የሠብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም የዘር ማጥፋትና የጦር ወንጀል እየፈፀመ ነው ብለዋል።
ይህ አሸባሪ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጥረት እያደረገ ቢሆንም በኢትዮጵያውያን አንድነትና ትብብር ጥረቱ እንደሚከሽፍ በየግንባሩ እያጋጠመው ያለው ሽንፈት እንደሚያሳይ ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.