Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ጤና ስትራቴጂው ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የዲጂታል ጤና ስትራቴጂው ጥራት ያለው፣ ፍትሃዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

የኢትዮጵያ የዲጂታል ጤና ስትራቴጂን ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጋር በማጣጣም በሚተገበርበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ጄነራል ዶክተር አብዮት ባዩ የዲጂታል ጤና ዋና አላማው ጥራት ያለው፣ ፍትሃዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል።

የዲጂታል ጤና ስትራቴጂው ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሰኬት ቁልፍ ሚና እንዳለው ዳይሬክተር ጄነራሉ ገልጸዋል።

ስትራቴጂን መሰረት ያደረገ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ቴከኖሎጂው የሚሰጣቸውን የእድገት እና የመሻሻል እድሎች አሟጦ ለመጠቀም እድል ከመስጠቱም በላይ በቴክኖሎጂው ሊመጡ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን አስቀድሞ በመለየት ለመቀነስ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

ሌሎች ዘርፎችም የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴርን ልምድ መነሻ በማድረግ እና ሃገራዊውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ የዘርፋቸውን ዝርዝር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ሊያወጡ ይገባል ተብሏል።

የዲጂታል ጤና ስትራቴጂው ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት እና የልማት አጋሮች በተገኙበት ወደስራ መግባቱ ይታወሳል።

በውይይቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን÷ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና አይሲቲ ሃላፊዎች ስለ ዲጂታል ጤና ስትራቴጂ ሰነዱ ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.