በምዕራብ አርሲ ለጀግናው ሰራዊት ከ39.4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ39 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተሰበሰበ።
የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የማትተካ ህይወቱን ሰውቶ ጠላትን እየተፋለመ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በዞኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
በ3 ሳምንት ውስጥ በተደረገው እንቅስቃሴ 39 ሚሊየን 410 ሺህ 273 ብር መሰብሰቡን የጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብዱራህማን ገመዳ ተናግረዋል።
በዚህ ድጋፍ ውስጥ የተሳተፉት የዞኑና የወረዳዎቹ አመራሮችና ሰራተኞች ከደሞዛቸው 15 ሚሊየን 88 ሺህ 596 ብር መለገሳቸውን ነዉ የተናገሩት።
አርሶ አደሮች 12 ነጥብ 7 ሚሊየን፣ ዩኒዬኖችና ህብረት ስራ ማህበራት 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።
ሴቶች 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ነጋዴዎች ደግሞ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸዉን አቶ አብዱራህማን ገልፀዋል።
በዚህ ዙር 33 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማሰባሰብ ታቅዶ ከ39 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ብር ማሰባሰብ ተችሏል ነው ያሉት።
በቢቂላ ቱፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!