በኮፐንሀገን በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴንማርክ ኮፐንሀገን ዛሬ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸነፉ።
በኮፐንሀገን ከተማ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች ግማሽ ማራቶን አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ በ59:10 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመጣት ሲያሸንፍ ፤አትሌት አቤ ጋሻሁን በ59:46 ሰዓት በመግባት 4ኛ ሆኖ አጠናቋል።
በሴቶች በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፀሃይ ገመቹ በ1:05:08 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ስታሸንፍ፤ አትሌት ሃዊ ፈይሳ በ1:05:41 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በሁለተኛነት ስታጠናቅቅ ፤አትሌት በየኑ ደገፋ በ1:08:15 ሰዓት 4ኛ ፣ አትሌት ይታይሽ መኮንን በ1:08:53 ሰዓት 5ኛ በመሆን ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!