የምዕራብ ጎንደር ህዝብ ለህልውና ዘመቻው ከ170 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎንደር ዞን ህዝብ 143 ሚሊየን 72ሺህ 869 ብር በጥሬ ገንዘብ፣ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ።
የዞኑ ህዝብ እንደሀገር የተቃጣውን ጦርነት ለመመከት ግንባር በመሄድ እያደረገ ካለው ተሳትፎ በተጨማሪ መከላከያውን ለማጠናከርና ደጀን ለመሆን የተለያዩ ተግባራትን እየተሰሩ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል።
በዕቅድ ደረጃ በዞኑ ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ለመሰብሰብ መታቀዱን የተናገሩት አስተዳዳሪው ህዝቡ በየትኛውም መልኩ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠይቋል።
በተያያዘ ዜና ዞኑ ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት በርካታ ወጣቶች ለስልጠና ማዘጋጀታቸውንም አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል።
ምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!