Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራን በመጠቀም የግብርና ምርትን ለማሳደግ አቀደች

 

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በግብርና ዘርፍ ከፍተኛ ምርት ለማስመዝገብ የዘርፉን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ተጠቃሚነት እንደምታጠናክር አስታወቀች።

ሲጂ ቲ ኤን እንደዘገበው የቻይና የግብርና ሳይንስ አካዳሚ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተደገፈ 14ኛ ዙር የአምስት ዓመት የልማት እቅዱን (2021-2025) ይፋ አድርጓል።

በእቅዱ መሠረት ቻይና በአምስት ዓመታት ውስጥ ቁልፍ የተባሉትን የምግብ ውስትናን የማረጋገጥ ፣ አረንጓዴ ልማትን የማስፋፋት፣ የሽታዎችን የመከላከልና የመቆጣጠር፣ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን የመጠቀም፣ መሰረታዊ የጥናትና ምርምር ስራዎችና የአካባቢ ልማት ተግባራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንደሚከናወኑ ተመልክቷል።

ቻይና እ.ኤ.አ በ2020 ያሳየችው የግብርና ቴክኖሎጂ የዕድገት መጣኔ ለጠቅላላ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት 60 በመቶ ድርሻ እንደነበረውም መረጃው ያመለክታል።

በአገሪቱ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን የመጠቀም ሀኔታም 96 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን የሀገሪቱ የግብርና ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ታንግ ሁዋጁን ያስታወቁት።

የተሻሻሉ የክብቶች ፣ የዶሮና የዓሳ ዝርያዎችን በዘመናዊ መንግድ በማርባት ምርቱ በየዓመቱ እያደገ እንዲሄድ መታቀዱንም ተናግረዋል ።

አካዳሚው ፕሬዚዳንት አክለውም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለቻይና የግብርና የኢኮኖሚ ዘርፍ አነቀሳቂሹ ሞተር ነው ብለዋል።

በቀጣይም በዘረመል ምርምር፣ በምርት ዕድገት፣ በበሽታ መከላከልና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማበልጸግ የግብርናው ዘርፍ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንደሚጠናከር ነው የጠቆሙት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.