Fana: At a Speed of Life!

በተማርነው የትምህርት መስክ ችግር ፈቺ ስራዎችን ለማከናወን ተዘጋጅተናል – ተመራቂዎች

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር በመቀየር ችግር ፈቺ ሰራዎችን ለማከናወን መዘጋጀታቸውን የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ተናገሩ።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ከዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች መካከል ድሮ ቶለሳ ከሥነትምህርት ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት የሜዳሊያና ዋንጫ ተሸላሚ ነው።

በሀገራችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት የሚሰጥበት ደረጃና የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን በትምህርት ጥራቱና ዘመናዊነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ይላል የሜዳሊያና ዋንጫ ተሸላሚው ድሮ ለኢዜአ በሰጠው አስተያየት።

በተለይም የቴክኖሎጂ-ትምህርት ጥምረት ለአንድ ሀገር ዕድገት ወሳኝ ነው የሚለው ድሮ፤ በዘርፉ በመሥራት ላስተዋላቸው ችግሮች የመፍትሔ አካል ለመሆን መዘጋጀቱን ገልጿል።

በሀገራችን የሕግ ጥሰቶችና ኢ-ፍትሐዊነቶች ይስተዋላሉ ያለው ደግሞ ከሕግ ትምህርት ቤት ከፍተኛነጥብ በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው በዳሳ ፈቃዱ ነው።

በኢትዮጵያ እውነተኛ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተማረው ትምህርት ችግር ፈቺ ስራዎችን በማከናወን የድርሻውን ለመወጣት ቁርጠኛና ለዚህም ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።

በሰስቴይነብል ናቹራል ሪሶርስ ማኔጅመንት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ የሆነችው ለምለም ዮሐንስም በበኩሏ፤ ሀገራችን በተፈጥሮ ሀብቶች የበለፀገች ብትሆንም ሀብቶቿን በመንከባከብና ያለ ብክነት ከመጠቀም ጋር ተያይዞ ክፍተት መኖሩን አስተውያለሁ ትላለች።

በዘርፉ የሚስተዋሉትን ክፍተቶች ለማስተካከል በተማረችበት የትምህርት መስክ ችግር ፈቺ ስራዎች ለማከናወን እንደምትጥር ገልጻለች።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.