Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ሰርጎ የገባው የጁንታ ሀይል እየተመታ ነው- የዞኑ አስተዳዳር

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በሶስት ቀበሌዎች ሰርጎ የገባውን የጁንታ ሀይል ከአከባቢው ለማስለቀቅ ከፍተኛ ተጋድሎ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳር ገለፀ፡፡

በወረባቦና በተሁለደሬ አካባቢዎች ሰርጎ ገብቶ የነበረው ሀይል ክፉኛ ተምትቶ መውጣቱን የገለጹት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ስይድ መሀመድ ÷ በደላንታ አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን የጠላት ሀይል ለመደምሰስ የጸጥታ ሀይሉ በከፍተኛ ወኔ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል።

የዞኑን ወጣቶች ከመከላከያ ጎን በስፋት ለማሰለፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና ጁንታው አማራ ክልልን ለቆ እስኪወጣና የህልውና ሰጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ተጋድሎው ይቀጥላል ብለዋል ።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.