Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ሰቃ ሆስፒታል አንድ እናት አራት እግር ያላትን ህፃን ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሰቃ ሆስፒታል አንድ እናት አራት እግር ያላትን ህፃን በሰላም መገላገሏ ተገለፀ።

እናት ገነት ፍሰሀ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ቤተሰብዎቿ ጋር ለመውለድ ነበር ወደ ጅማ ዞን ሸቤ ወረዳ የሄደችው።

ሀሙስ ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም ምጥ በርትቶባት ወደ ሰቃ ሆስፒታል የተወሰደችው ገነት የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ባደረጉላት ድጋፍ አራት እግር ያላትን ህፃን በሰላም መገላገል መቻሏን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አዳነ ዴሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ የኮርፖሬት ተናግረዋል።

እናት ገነት በሰላም እንድትገላገል የህክምና ድጋፍ ሲያደርግላት የነበረው የጤና ባለሙያ ወንድሙ ለማ፥ ከወገብ በላይ የሰውነት አካል የሌለው ወንድ ህፃን ሙሉ የሰውነት አካል ያላት ሴት ህፃን ተጣብቆ መወለዱን ተናግሯል።

የህፃኗ ጤንነት ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሆነ የጠቆመው የጤና ባለመያው፥ ለተጨማሪ እርዳታና ምርመራ ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል መላኳን ገልጿል።

የሰቃ ሆስፒታል ባለሙያዎች እናቷን ለማዋለድ አንድ ሰዐት እንደፈጀባቸው ከሰቃ ሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሙክታር ጠሃ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.