ሁለተኛው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተቋቋመ
አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አቋቋመ።
በሥነ-ስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ስልት በመከተል ምሁራን እና ተማሪዎች ለሀገራቸው የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ የሚያግዝ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል፡፡
ምሁራን እና ተማሪዎች ይህን የቴክኖሎጂ መዋቅር በመጠቀም በዲጂታል ዲፕሎማሲ ወቅቱ የሚጠይቀውን ሀገራዊ ትግል እንዲያደርጉም ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
በእለቱም ሁሉንም ዩኒቨርሲቲዎች እርስ በእርስ የሚያገናኘው የአባይ ልጆች በተሰኘ ሶፍትዌር ላይም ምሁራንና ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያደርጉ ተደርጓል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ምሁራንና ተማሪዎች በአባይና በሌሎች ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ የዲጂታል ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማለም ይፋ የተደረገ ፕሮጀክት ሲሆን ቦንጋ ከወላይታ ሶዶ በመቀጠል ማዕከሉን ያቋቋመ ሁለተኛው ዩኒቨርሲቲ ሆኗል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!