አልማ በቀጣይ በአቅም ግንባታና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋም ላይ እንደሚሰራ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልማት ማህበር በ2014 ዓ.ም ከተሰማራበት የዘላቂ ማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን አቅም ግንባታና ለተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ ማቋቋም ተግባር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡
ልማት ማህበሩ ስትራቴጅያዊ የለውጥ ዕቅዱ በበርካታ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ በተለዋዋጭ የመፈፀም ስልት የተከናወነ መሆኑን የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ገልፀዋል፡፡
ከ2014 ዓ.ም ዋና ዋና ተግባሮች መካከል አባላት ማፍራት÷ ሀብት ማሰባሰብና የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችን ማጠናከር መሆኑንም ተናግረዋል።
በተጨማሪም የ2014 ዓ.ም ዕቅድን በላቀ ሁኔታ ማስፈፀም፣ ማህበሩን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ተቋማዊ ሽግግር ማድረግ፣ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችን መስራት ትኩረት ተሰጥቶት ይተገበራል ብለዋል፡
፡
አልማ ከክልል ውጭና ከዳያስፖራው ጋር በሚደረግ የልማት ሀብት ማሰባሰብና መልሶ መቋቋም ተግባራት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን ከአማራ ልማት ማህበር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!