በአገው ግምጃ ቤት ለሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ ሚሊሻዎች ተመረቁ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደር ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ሚሊሻዎች አስመረቀ፡፡
ሚሊሻዎቹ የክልሉ መንግስት ያቀረበውን የክተት ጥሪ ተከትሎ ለህልውና ዘመቻ ለመቀላቀል ለሁለተኛ ዙር ለ15 ቀናት መሠረታዊ የውትድርና ሙያ የሰለጠኑ ናቸው፡፡
በምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ደመላሽ መኮነን ሁላችንም አሸባሪውን የህወሓትን ወረራ ለመመከት ልዩነታቸውን በመተው በአንድነት በመቆም የክልላችንንና የአካባቢያችንን ሰላምና ደህንነት ማስከበር አለብን ብለዋል፡፡
ተመራቂ የሚሊሻ አባላት በበኩላቸው÷ አሁን በክልሉ ብሎም በሃገሪቱ ላይ አሸባሪው ህወሓት ቡድን የሚያደርገውን ወረራ ለመመከትና ለመደምሰስ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ከአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ጋር ተቀላቅለው ለመዝመት ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከአንከሻ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!