Fana: At a Speed of Life!

ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበራ አሬራ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ ረፋድ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተካሄደ አሰሳ በሃዋሳ ከተማ በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ታቅዶ የነበረና የህትመት ሂደቱ ያላለቀ ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን አስታውቀዋል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ለማጣራት ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በሆቴል ውስጥ የሚያትሙትን ሀሰተኛ ዶላር የሚገዛ ሰው ሲያፈላልጉ እንደነበር ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፤ የህብረተሰቡና የሆቴል ባለቤቶቹ ጥቆማ ለግለሰቦቹ መያዝ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.