Fana: At a Speed of Life!

ከማዕድናት እና ከከበሩ ድንጋዮች 682 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት አመት ከማዕድናት እና ከከበሩ ድንጋዮች 682 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህ ወቅት በበጀት አመቱ ማዕድናት እና የከበሩ ድንጋዮች 682 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ሚኒስትር ዲኤታዋ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ እና ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ ወርቅ 9 ሺህ 384 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሄራዊ ባንክ በማቅረብ 671 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ሲገኝ፥ ታንታለምን ጨምሮ ከተለያዩ ማዕድናት የከበሩ ድንጋዮች ደግሞ ከ10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ መገኘቱን ገልጸዋል።

በቀጣዩ በጀት አመት የወርቅ ምርትን በማሳደግ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት መታቀዱም ተገልጿል።

ለዚህም የተሻለ የወርቅ ምርት የሚገኝባቸው ተብለው በተለዩ አራት ክልሎች ላይ ከወርቅ አምራቾች ጋር የተሻለ ምርት ለማግኘት እየተሰራ ነው ተብሏል።

ከብረት ማዕድን ጋር በተያያዘም ምርቱ በስፋት ይገኝባቸዋል በተባሉት አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጤታማ ስራ ለመስራት ማቀዱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ነዳጅን በሚመለከት 37 የነዳጅ ፍለጋ ብሎኮች የተለዩ ሲሆን፥ ሰባት የነዳጅ አውጭ ኩባንያዎች ፈቃድ ወስደው በስራ ላይ መሆናቸውንም ገልጿል።

በኦጋዴን 65 ፣ በደቡብ ኦሞ አራት እንዲሁም በጋምቤላ ሁለት በድምሩ 71 ጉድጓዶች ተቆፍረዋልም ነው ያለው።

ከተፈጥሮ ጋዝ ጋር በተያያዘም የተረጋገጠ የተፈጥሮ ጋዝ በተለይም በፖሊ ጂሲኤል ፍቃድ ስር 6 ነጥብ 4 ትሪሊየን ኪዩብ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማት እየተሰራ መሆኑንም ነው የገለጸው።

በተጨማሪም ሚኒስቴሩ በዛሬው መርሃ ግብሩ አንዱ የሆነውን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን በተለያዩ መንገድ የተባበሩ አካላትን የምስጋና መርሃ ግብር አከናውኗል።

በዚህም የቀድሞ የተቋሙ ሚኒስትሮች፣ የስራ ሃላፊዎችን እና በዘርፉ በተለያዩ ስራ ላይ እና በተቋሙ የህንጻ እድሳት አስተዋጽኦ ላደረጉ ኩባንያዎች የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም ተከናውኗል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.