ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፊታችን ሰኞ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰኞ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፊታችን ሰኞ ልዩ ስብሰባውን ያካሂዳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ በዕለቱ የ11ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አመላክቷል።