Fana: At a Speed of Life!

የዋጋ ንረቱ ኢኮኖሚያዊ ጦርነት በመክፈት ሀገርን የማዳከም ሴራ ነው – ዶክተር ተሾመ አዱኛ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተስተዋለ የሚገኘው የዋጋ ንረት ፖለቲካዊ ጉልበትን ለማግኘት የሚደረግ ሙከራና፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የኢኮኖሚ ጦርነት በመክፈት ሀገርን የማዳከም ስልት እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ዶክተር ተሾመ አዱኛ ገለፁ፡፡

ዶክተር ተሾመ÷ የዋጋ ንረት የፍላጎትና ዋጋ አለመመጣጠን፣ በቂ መረጃና በቂ አቅርቦት አለመኖርና የማምረቻ ዋጋ መጨመር የሚያስከትለው የዋጋ ጭማሪ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

በኛ ሀገር እየሆነ ያለው ግን ከዚህ በተለየ መልኩ ኢኮኖሚውን አደጋ ውስጥ የመክተት አሻጥር ነው ብለዋል።

አሁን የሚስተዋለው የዋጋ ንረትም ከገበያው ፍላጎት ጋር የማይገናኝ እንደሆነ ጠቁመው መንግሥት ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ክትትል በማድረግ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.