የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ አዋጆችና ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባዔ አዋጆችንና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።
ምክር ቤቱ ለአራት ቀናት ያካሄደውን ጉባዔ ዛሬ ሲያጠናቅቅ ሁለት ረቂቅ አዋጆችንና የስምንት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።
ጉባዔው ያጸደቃቸው አዋጆች የክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤቶችን በአዲስ ለማዋቀር የቀረበውንና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሰራተኞች የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማሻሻያ ናቸው።
በተጨማሪ በምክር ቤቱ ከተሾሙት ዳኞች መካከል አራቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ የሰበር ሰሚ ችሎት ዳኞች መሆናቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!