በሀረሪ ክልል ለቀድሞ ምልስ ሰራዊት አባላት ሽኝት ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃረሪ ክልል የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ የቀድሞ ምልስ ሰራዊት አባላት ሽኝት ተደረገ።
ከዚህ ቀደም የሀገርን ዳር ድንበር ሲያስከብሩ ቆይተው እና ግዳጃቸውን አጠናቀው ተመልሰው በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የቆዩ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበል በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ምልስ የሰራዊቱ አባላት ጥሪውን ተቀብለው ሰራዊቱን ለመቀላቀልና ሀገርን በማዳን ተግባሩ የመሳተፍ እድል በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
የሀረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ናስር ዩያ በሽኝት መርሃግብሩ እንደተናገሩት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከተለያዩ የውስጥ የውጭ አካላት ጋር በመቀናጀት እና ሀገር ለመበተን የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል።
ሆኖም ግን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከክልል የፀጥታ ሀይላት ጋር በመቀናጀት በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ እየመከቱ ይገኛሉ ማለታቸውን ከሃረሪ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሰራዊቱን ለተቀላቀሉ አባላትም እንደቀድሞው ሁሉ ግዳጃቸውን በብቃት እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የክልሉ መንግስትም ሀገር ለማዳን ተግባር ለሚሳተፉ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!