Fana: At a Speed of Life!

በጉና አካባቢ አርሶ አደሮች ህወሓትን ለሶስት ቀናት በመዋጋት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ጉና አካባቢ አርሶ አደሮች የህወሓት የሽብር ቡድንን ለሶስት ቀናት በመዋጋት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ገለጹ።

የሽብር ቡድኑ ጉና ተራራን እንደ መስፈንጠሪያ ተጠቅሞ ወደ ደብረ ታቦር እና እስቴ ለመግባት በማሰብ ወረራ ለመፈፀም ሲያስብ አርሶ አደሮቹ ከየቀበሌው በመውጣት በራሳቸው ትጥቅ ለሶስት ቀናት በመዋጋት በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ድል አስመዝግበው ወደ መጣበት እንደላኩት በስፍራው ለሚገኙ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በውጊው ወቅት አንድ የጦር አዋጊ የማረኩ ሲሆን አሁንም አካባቢያቸውን በንቃት እንደሚጠብቁም ነው የተናገሩት።

መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ለአካባቢው በማድረግ ቡድኑ ህልውናውን እስከሚያጣ ድረስ እንፋለማለንም ብለዋል።

ጁንታው ለሶስት ቀናት በቆየባቸው ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎች ሴት ወንዱ አዛውንቶች ሁሉ በመተባበር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እንደቀጡት እና በአካባቢው የተለያዩ መሸንገያዎችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ለመጠቀም ቢሞክርም ህዝቡ በአንድነት በመቆም ደማቅ ድል እንዳስመዘገበም ጠቁመዋል።

በጉና ተራራ በነበረው የዋንቃ ግንባር በእስቴ ወረዳ የሚገኙ የዳት፣ ጥናፍ፣ የአንጋጫት፣ የእለት፣ ዶስካ እና የድባና አርሶ አደሮች እና ነዋሪወች ተሳትፈዋል።

በምንይችል አዘዘው እና ዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.