Fana: At a Speed of Life!

የትህነግን ወረራ ለመመከት መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ ጀግኖች መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል – አቶ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ትህነግ ወረራ ለመመከት መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ ጀግኖች መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በክምር ድንጋይ 11 የአሸባሪውን ትህነግ አባላት የረፈረፉትን አቶ ጌጤ መኳንንትን አግኝተው አበረታተዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ጉና ቤጌምድር ወረዳ ክምር ድንጋይ ከተማ ያፈራቻቸው የወቅቱ ጀግና ናቸው አቶ ጌጤ መኳንንት-አባ ረፍርፍ፡፡

አሸባሪው ትህነግ በደቡብ ጎንደር ዞን ክምር ድንጋይ አካባቢ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥቃት ሲያደርስ አቶ ጌጤ ለሕዝባቸው መስዋዕት መሆን እንደሚገባ ቀድመው ራሳቸውን አሳምነዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ከሆቴላቸው ገብተው በቀጭን ትዕዛዝ የሚፈልጉትን ሲያስቀርቡ አባ ረፍርፍ 11ዱን እስከወዲያኛው በመሸኘት ወደ ጫካ ገብተው አኩሪ ጀብድ ፈጽመዋል።

የዘመኑ የአማራ ሕዝብ ማንነትና አኩሪ ታሪክ አንዱ ማሳያ የሆኑት አቶ ጌጤን የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር አግኝተው አበረታተዋቸዋል።

አቶ ጌጤ አሸባሪው ትህነግ የአማራን ሕዝብ ማንበርከክ እንደማይችል እኔ ህያው ምስክር መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር በዚህ ወቅት፥ አሸባሪው ትህነግ ወረራ በፈጸመባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ዘረፋና ጥቃት እየፈጸመ ሲመጣ ሕዝቡ ኢትዮጵያን ለማዳን ከተሰለፈው ሠራዊት ጋር ተባብሮ በመታገል ብዙ ጀግኖች አይተናል ብለዋል።

አቶ ጌጤን ጨምሮ ለአማራ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ህልውና እየተዋደቁ ላሉ ጀግኖች መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ርእሰ መሥተዳድሩ አረጋግጠዋል።

“የሽብር ቡድኑ ዓላማ ሕዝባችንን በማንበርከክ ኢትዮጵያን ማፍረስ በመሆኑ ህልውናውን እስከማክሰም የሚደርስ ትግላችን ይቀጥላል፤ የአማራ ሕዝብም እያሳዬ ያለውን አኩሪ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል አለበት” ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.