በባህርዳር ከተማ በ550 ሚሊየን ብር የተገነባው ኦፕሬሽናል ዴፓ ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ከተማ በ550 ሚሊየን ብር የተገነባው ኦፕሬሽናል ዴፖ ተመረቀ።
የቤአኤካ ጠቅላላ የንግድ ስራዎች ድርጅት እህት ኩባንያ አካል የሆነው ኢሌ ኦፕሬሽናል ዴፖ ነው ዛሬ የተመረቀው።
ዴፖው 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በቀን 700 ሺህ ሊትር የማደል አቅም እንዳለው የቤአኤካ ዋናስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ምስጋናው ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አበባው ውቤ በበኩላቸው፥ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥረውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ለመፍታት የአዳዲስ ኦፕሬሽናል እና ሌሎች ማደያዎች እየተገነቡ ነው ብለዋል።
በክልሉ 100 የሚደርሱ ዴፖዎች እና ከ800 በላይ ማደያዎች እንዲገነቡ አቅጣጫ ተቀምጦ ለዴፖዎች እና ማደያዎች ግንባታ የሚሆን ቦታ ለባለሀብቶች ተሰጥቷል ነው የተባለው።
የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በከተማዋ የሚታየውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ይህ ዴፖ ወደስራ መግባቱ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።
ለማደያ ግንባታ ቦታ የወሰዱ ባለሀብቶች በፍጥነት ወደስራ እንዲገቡ ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!