ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚደረግ የታክስ ስወራን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ተደርጓል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታውን እንደአጋጣሚ በመጠቀም የታክስ ማጭበርበር ለማድረግ የሚሞክሩ አንዳንድ ድርጅቶች መኖራቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለዚህም ከፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርምራ እና ከዐቃቤ ህግ ጋር በጋራ በመሆን የታክስ ማጭበርበር ድርጊት የሚያከናውኑትን ለመከላከል በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል።
እነዚህ ድርጅቶች ከጁንታው ተለይተው ስለማይታዩ ጠንከር ያለ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን የታክስ ህግ ተገዥነት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የሚኒስቴሩ ሠራተኞች 77 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ከደመወዛቸው ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እና የደም ልገሳ ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!