ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የፍቅር ያሸንፋል በጎ አድራጎት ማህበር አባላት ሽኝት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀገርን ህልውና ለማስከበር በግንባር ለመሰለፍ ዝግጁ ለሆኑ የፍቅር ያሸንፋል በጎ አድራጎት ማህበር አባላት ሽኝት ተደረገላቸዉ።
የማህበሩ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚስባህ ከድር ፥ እንደ ሌሎች ማህበራትና ሀገር ሽማግሌዎች ዕርቅ እንዲወርድ እና ሁሉ ነገር በፍቅርና በይቅርታ እንዲታለፍ መቀሌ ቢሄዱም አለመሳካቱን ተናግረዋል።
እኛ ኢትየጵያውያን እያለን ኢትየጵያ አትፈርስም በማለት ሀገር ለመታደግ ቀጣይ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎችም በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጁ ነን ብለዋል።
የመከላከያ ሚዲያ ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብ/ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳ በበኩላቸው ፥ የፍቅር ያሸንፋል ማህበር ለሚሠራው በጎ ተግባር ምስጋና አቅርበው ፣ ጁንታው ለራሱ ጥቅም ሲል በሠራዊቱና በህዝቡ ላይ ይቅር የማይባል ክህደት ፈጽሟል ሲሉ ተናግረዋል።
አሸባሪው ህወሓት ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ ቢነሳም አንድ አድርጎናል ፣ ይህ ሀገራዊ አንድነትም ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል ።
ለሠራዊቱ ደጀን ለመሆን ወደ ግንባር ለሚዘሚቱ 50 ወጣቶች በድል እንዲመለሱም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ፣ የማህበሩ አባላት ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የትግራይ ክልል ተወላጆች እና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮችም የተገኙ ሲሆን ፥የትግራይ ዲሞክራስያዊ ፓርቲም አሸባሪውን ጁንታ ቡድን ለመደምሰስ ከፍቅር ያሸንፋል ማህበር አባላት ጋር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!