የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና የወግዲ እና የጃማ ወረዳዎች ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ከወር ደመወዛቸው ለህልውና ዘመቻው የወር ደመወዛቸውን ድጋፍ አደረጉ፡፡
ከወር ደመወዛቸው ድጋፍ በተጨማሪ በተለያዩ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ አሸባሪውንና ወራሪውን የትህነግ ቡድን በግንባር ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋርዳቸው ወርቁ፥ ዩኒቨርሲቲውና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል እና ሚሊሻ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ፣ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ለህልውና ዘመቻው ደጀንነቱን እያረጋገጠ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ማኀበረሰብ በሕልውና ዘመቻው በሚከናወኑ ተግባራት ለሚቀርብለት ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ያደረገው ወረራ የኖረበት የባንዳነት ታሪኩን ገሃድ ያወጣበት ነው ብለዋል፡፡
መላው የክልሉ ሕዝብም በአንድነት በመቆም የአሸባሪ ቡድኑን ሀገር የማፍረስ ሴራ ሊያከሽፍ እንደሚገባ ማስገነዘባቸውነ አሚኮ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ በደቡብ ወሎ ዞን የወግዲ እና የጃማ ወረዳዎች ለሕልውና ማስከበር ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ።
አሸባሪው ትህነግ እየፈጸመ የሚገኘውን ወረራ ለመመከት በግንባር ለሚፋለሙ የቁርጥ ቀን ጀግኖች የሚሆን ድጋፍ ከተለያዩ አካባቢዎች እየደረሰ ይገኛል።
የወገዲ ወረዳ ነዋሪዎች ለህልውና ዘመቻው 14 ሰንጋዎችን እና ስንቅ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለሚሊሻ እና ፋኖ ድጋፍ አድርገዋል።
በተመሳሳይ የጃማ ወረዳ ነዋሪዎች 15 የእርድ ሰንጋዎችንና ደረቅ ሬሽን ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።
የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ ለህልውና ዘመቻው የተለያዩ ወረዳዎች፣ ተቋማትና ግለሰቦች እያደረጉት ያለው ድጋፍ የአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ግብዓተ መሬት ያፋጥናል በመሆኑ ድጋፉም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!