የአሸባሪው ጁንታ ሀገር የማፍረስ ጥረት በፀጥታ አካላት ከንቱ ይሆናል – የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ጁንታ ሀገር ለማፍረስ የሚያደርገው ጥረት በፀጥታ አካላት ከንቱ ይሆናል አሉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ፡፡
የወላይታ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ከተለያዩ የፀጥታ አካላትና ባለድርሻዎች ጋር የስራ ሂደቱን በተመለከተ እያካሄደ በሚገኘው የንቅናቄ መድረክ ላይ ዋና አስተዳዳሪው ይህንን የተናገሩት፡፡
በዞኑ የሰላምና ፀጥታ ስራው እንዲሳካ ያደረጉ የፀጥታ አካላትን በተለይ አሸባሪው ጁንታ በሀገራችን ጦርነት በከፈተበት ወቅት አከባቢያችሁን በመጠበቃችሁ የዞኑ መንግስት ያመሰግናችኀል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው።
በየጦር ግምባሩ ለሀገራቸው የሚዋደቁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን ከማመስገን በዘለለ በተለያየ መንገድ ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል ብለዋል።
የዞኑ መንግሥት ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሰራዊት አባላት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በጥላሁን ሁሴን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!