Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማና ደቡብ ክልሎች በግብርና ዘርፍ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዩኒየኖች እዉቅናና ሽልማት ተሰጠ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የደቡብ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በሲዳማና ደቡብ ክልሎች በግብርና ዘርፍ የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ የህብረት ስራ ዩኒየኖች እዉቅናና ሽልማት ሰጠ።

በ2013 በጀት አመት የግብርናዉን ዘርፍ ፋይናንስ በማድረግና በኩታ ገጠም እርሻ ዉጤታማ የሆኑ 29 ማህበራት 36 ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ተሸላሚ ሆነዋል።

የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ ፈጠነ ኤጀንሲው በዋናነት የግብርናዉ ዘርፍ ማነቆዎችን ለመፍታት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሲዳማም ሆኑ የደቡብ ክልል አርሶ አደሮች ወደ ዘመናዊ የግብርና ስራ የሚያደርጉትን ሽግግር ለማፋጠን ድርጅቱ በብድርና ቁጠባ እና በገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየኖች በኩል ሙያዊና ቁሳዊ ድጋፎችን እያደረገላቸው እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ተግዳሮቶችን ለመፍታት የብድርና ቁጠባ እና የግብርና ህብረት ስራ ዩኒየኖች በኩል ተግዳሮቶቹን የመፍታት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ነዉ የገለፁት።

ጣቢያችን ያነጋገራቸው የማህበራቱ አባላት ፥ያገኘነው እዉቅናና ሽልማት የበለጠ ለስራችን ትኩረት እንድንሰጥ አድርጎናል ብለዋል።

በቢቂላ ቱፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.