ሸኔን የሚቃወም ሰልፍ በአሰላ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሸኔን የሚቃወም እና መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በአሰላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ከአርሲ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች እንዲሁም ከአሰላ ከተማና አካባቢዋ የተውጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰልፉ ተሳትፈዋል፡፡
ሰልፈኞቹ ‘’የሃገራችን ብልፅግና በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን አይደናቀፍም፣ ወያኔን ባስወገደው የተባበረ ክንዳችን ሸኔን እንነቅላለን፤ ለኢትዮጵያ እዘምታለሁ የትም መቼም በምንም፤ ሸኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው’’ የሚሉ መልዕክቶች አስጋብተዋል፡፡
በዮናታን ብርሃኑ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!