ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በኢትዮጵያ ከቻይና ኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የቻይና ኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ያንግ ይሃንግ ጋር ተወያዩ።
ውይይታቸው በትራንስፖርት ዘርፍ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በውይይታቸውም በዋናነት የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት ጋር ከዚህ በፊት የጀመራቸውን የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራን የማጠናከር፣ በባቡር መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ እንዲሁም የሎጀስቲክስ ውጤታማነትን ከማሻሻል ረገድ በጋራ ለመስራት ተግባብተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!