የጎሀ ፂዮን ደጀን መንገድን በነገው እለት አገልግሎት ለማስጀመር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በናዳ ምክንያት የተዘጋውነን ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም የሚወስደውን መንገድ በነገው ዕለት በከፊል ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ የመንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በተከሰተ ናዳ ካሳለፍነው ዓርብ ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል፡፡
መንገዱን የዘጋውን ቋጥኝ ለማንሳት በአማካይ በአንድ ጊዜ እስከ 20 ድማሚት በመጠቀም 10 ጊዜ በላይ ድማሚት በማፈንዳት መንገዱን የመክፈት ስራ እየተሰራ ነው፡፡
አሁን ላይም መንገዱ ላይ የነበረውን የቋጥኝ ናድ 75 በመቶ መቀነስ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
ተጨማሪ መንሸራተት ካላጋጠመም አሁን ባለው አካሄድ እስከ ነገ ድረስ ቢያንስ አንድ ተሽከርካሪ ማሳለፍ የሚያስችል ስራ ለመስራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሃይለኢየሱስ ስዩም