የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በደባርቅ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጎንደር ቅርንጫፍ የህወሓት አሸባሪ ቡድን በፈጸመው ወረራ ተፈናቅለው በደባርቅ ጊዜያዊ መጠለያዎች ለሚገኙ ወገኖች የምግብና የሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
የማህበሩ ቅርንጫፉ አስተባባሪ አቶ አታለል ታረቀኝ ለኢዜአ እንደተናገሩት ድጋፉ የተደረገላቸው በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ሳቢያ ከማይጸብሪና አዲ አርቃይ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለመጡ 1 ሺህ ለሚደርሱ አባወራና ቤተሰቦቻቸው ነው፡፡
ለእነዚህ ወገኖች 8 ቦንዳ የአዋቂና የህጻናት አልባሳት እንዲሁም ሃይል ሰጪ ብስኩቶች እና 980 የውሃ መቅጃ ጄሪካኖች ነው የተሰጠው።
በተጨማሪም ለተፈናቃዮቹ የግል ንጽህና መጠበቂያ የሚውሉ 10 ሺህ የሚሆኑ የልብስ ሳሙናዎች ድጋፍ መደረጉንም አስተባባሪው ተናግረዋል።
ማህበሩ በቀጣይም በደባርቅ ከተማ በጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ ለሚገኙ ሌሎች 3 ሺህ ለሚደርሱ ተፈናቃይ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!