Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በጀግንነት እናስከብራለን – ምልምል ወታደሮች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓትን አሸባሪ ሃይል በማጥፋት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በጀግንነት ለማስከበር መዘጋጀታቸውን በጦላይ ማሰልጠኛ ማዕከል መሰረታዊ ውትድርና የሚሰለጥኑ ምልምል ወታደሮች ገለጹ።

ከብሔራዊ ቴአትርና ከኦሮሚያ ባህል ማዕከል ቢፍቱ ባንድ የተውጣጡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጦላይ ማሰልጠኛ ማዕከል ለሚገኙ ምልምል ወታደሮች ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው ምልምል ወታደሮች በሰጡት አስተያየት፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመዳፈር የተነሳን ሃይል በመመከት ድል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ድል በማድረግ የሃገርንና የህዝብን ህልውና እናስጠብቃለንም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የጣሉባቸውን ኃላፊነት የደም መስዋዕትነት በመክፈል አሸባሪ ሃይሎችን ለማጥፋት በቆራጥነት ደሚታገሉም ገልጸዋል።

“ቅድመ አያቶቻችን በክብር ያቆዩልንን ሃገር ለወራሪ አንሰጣትም፤ እኛም በደምና አጥንታችን አስከብረን እናቆያታለን” ብለዋል ሰልጣኞቹ።

በኢትዮጵያ ላይ ሊቃጣ የሚችል ጠላትን ተዋግቶ ለማሸነፍ የሚያስችል ስልጠና እየወሰዱ መሆኑንም ነው ምልምል ወታደሮቹ የገለጹት።

ሰልጣኞቹ በየትኛውም መልኩ በኢትዮጵያ ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶችን በመመከት ድል ማድረግ የሚያስችል ወታደራዊጥበብ እየተማሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለምልምሎቹ ስራዎቻቸውን ያቀረቡት ከያኒያን በቀጣይ እስከ ግንባር ድረስ በመዝመት የሰራዊት ደጀንነታቸውን የማስቀጠል ፅኑ አቋም መያዛቸውን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.