Fana: At a Speed of Life!

እርዳታ ድርጅቶች የሰብዓዊ ድጋፎችን በፍትሃዊነት ሊያደርሱ ይገባል – በደሴ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ከውግንና በመውጣት የሰብዓዊ ድጋፎችን በፍትሃዊነት ማድረስ እንዳለባቸው በአሸባሪው ህወሃት ምክንያት ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የሚገኙ ዜጎች ጠየቁ።

የአሸባሪው ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ በመግባት ዝርፊያ፣ ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

ከራያ ቆቦ፣ አላማጣና ሌሎች አካባቢዎች በቡድኑ ትንኮሳ የተፈናቀሉ ወገኖች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት የህወሃት ሰርጎ ገቦች በንፁሃን ላይ አሰቃቂ ወንጀሎችን ፈፅሟል።

ቡድኑ የከፈተውን ጥቃት ሽሽት ከሞቀ ቤት ንብረታቸው ርቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ነው የተገለፁት፡፡

ነፍሳቸውን ቢያተርፉም ቤት ንብረታቸው በቡድኑ መዘረፉን፣ ቤተሰቦቻቸው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ለችግር መዳረጋቸውን አስረድተዋል።

የትኛውም ዓለምአቀፍ የእርጋታ ድርጅት እንዳልደረሰላቸው ገልጸው÷ ይህም በድርጅቶቹ ላይ የፍትሃዊነት ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓቸዋል።

በዚህም ዓልሚ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ህፃናት፣ ወለል ላይ ሲተኙ የሚያጋጥማቸው ቅዝቃዜና እንግልት የዓለምአቀፍ ተቋማቱ ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓቸዋል፡፡

በደሴ ከተማ ከ55 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በስምንት ማዕከላት የተጠለሉ ሲሆን አሁን ጊዜያዊ መጠለያ የሆኑት ትምህርት ቤቶች ናቸው።

መንግስት ድጋፉን እንዲያጠናክር የጠየቁት ዜጎች ዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅቶችም ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ይልቅ ሰብዓዊነትን እንዲያስቀድሙ ጠይቀዋል።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.