ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመስጠት ለሚንቀሳቀሱ ለኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ሽኝት ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመስጠት ለሚንቀሳቀሱት ለኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ሽኝት አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሯ የኪነጥበብ ዘርፍ የኢትዮጵያ አንድነት ከማስጠበቅ አንፃር ከጥንት ጀምሮ ትልቅ አበርክቶ ነበረው ብለዋል።
ኢትዮጵያዊነትን በእያንዳንዱ ኢትዩጵያዊ ልብ ውስጥ ከመትከል አንፃርም ዘርፋ ሚናገረውን በሚገባ ስለመወጣቱም አንስተዋል።
አሁንም ሀገር ላይ ከተደቀነው አደጋ እና ብሄራዊ አንድነታችንን ከማስጠበቅ አንፃር ብዙ ይጠበቅባቸዋል ያሉት ሚኒስትሯ መንግስት በሁሉም ነገር ከጎናችሁ ነው ብለዋል።
የኪነጥበብ ባለሞያዎቹ ጉዟቸውን ወደ ጦላይ እና አዋሽ አርባ ማሰልጠኛ እያደረጉ ነው።
በአዋሽ አርባ እና በጦላይ ማሰልጠኛ ማዕከል በርካታ ወጣቶች የሀገርን ጥሪ ተቀብለው መከላከያውን ተቀላቅለዋል፡፡
የኪነጥበብ ባለሙያዎችም እነሱን ለማበረታታት እና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ስፍራው መጓዝ ጀምረዋል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ እና ታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!