Fana: At a Speed of Life!

የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ መምህራንና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደሞዛቸውን አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ መምህራንና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደሞዛቸውን አበረከቱ።

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሽብርተኛውን  ቡድን ለመደምሰስ በሚያደርጉት ጥረት ከጎናቸው ነን ያሉት ሠራተኞቹ፥ ከገንዘብ ድጋፉ ባለፈም ደማቸውን ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ለግሰዋል።

“ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ላይ መልክታቸውን ያስተላለፉት የዪኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰለሞን ዘሪሁን፥ ሀገራችን ያጋጠማትን የህልውና ጥያቄ በማያዳግም መልኩ ለመመለስ ሠራዊቱ በሚያደረገው ጥረት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ያለውን አጋርነት ለማሳየት የአንድ ወር ደሞዛቸውን መለገሳቸውን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም በእውቀት፣በገንዘብና በቁሳቁስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.