Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በጎርፍ አደጋ የአንድ ቤተሰብ ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በደራሽ ጎርፍ አደጋ የአንድ ቤተሰብ ሕይወት አለፈ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ግዛቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ የጎርፍ አደጋው የተከሰተው በሞረትና ጅሩ ወረዳ ጅሁር አካባቢ ጃትና ይቆሮ ቀበሌ ልዩ ቦታው ይዜዮ ከተባለው ስፍራ ነው።

ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓመተ ምህረት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት በጣለው ከባድ ዝናብ ከስራ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የነበሩ እናት አባትና ልጅ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት ጉድበር ወንዝ ሞልቶ በደራሽ ጎርፍ ተወስደዋል ብለዋል።

በፍለጋ የሶስቱም ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ተናግረዋል።

የክረምቱ ወቅት ዝናቡ እየከበደ የመጣበት በመሆኑ ሕብረተሰቡ አቋራጭ መንገዶችን ከመጠቀም ይልቅ ድልድዮችን መጠቀም እንዳለበት ጠቁመው፥ ለመብረቅ አደጋ አጋላጭ ከሆኑ ሁኔታዎችም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮማንደር ተስፋዬ አሳስበዋል።

በሰላም አሰፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.