ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን በማስመልከት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የውይይት መድረክ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን በማስመልከት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ቀን ሲካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ችግኝ በመትከል ተጠናቀቀ።
ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን ለመገደብ በተለያየ ጊዜ ብትሞክርም ሳይሳካላት መቅረቱን ያስታወሱት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዑባህ አደም፥ ይህ ትውልድ ወንዙን ለመገደብ በሚያደርገው ጥረት ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የፖናል ውይይት ማዘጋጀት እዳስፈለገው ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ መሀመድ አህመድ ቡኽ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ልትበለፅግ የምትችለው አባይን የመሠሉ የተፈጥሮ ሀብቶቿን መጠቀም ስትችል መሆኑንን ገልጸዋል።
የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የፖናል ውይይቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ የዲፕሎማሲ ድል ባገኘችበት ማግስት መካሄዱ ለየት እንደሚያደርገው አንስተዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ የዲፕሎማሲ ስራ ማከናወን ይጠበቅበታል ብለዋል።
የግድቡን ግንባታ ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለው ተፅንኦ ከግድቡ በላይ ነው ያሉት ደግሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ናቸው።
ግድቡ ከአድዋ ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያውያን በአንድነት እንዲቆሙ ያደረጋቸው መሆኑንም አስረድተዋል።
በአድዋ ኢትዮጵያ ከፖለቲካ ጥገኝነት መላቀቋን የገለፁት ዶክተር አረጋዊ፥ በህዳሴ ግድብ ከምዕራባውያን የኢኮኖሚዊ ጥገኝነት ለመላቀቅ የጀመረችው ጉዞ ከጠላቶቿ ዘንድ መልካም መልስ እያስገኘ ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለግድቡ ዘብ መቆም እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!