Fana: At a Speed of Life!

የልዩ ዞኑ አርሶ አደሮች በ12 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ማህበር መሰረቱ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን አርሶ አደሮች በ12 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል “ጃራ ሚልኪ የገበሬዎች አክሲዮን ማህበር ” መስርቱ፡፡

የምስረታ ስነ ሥርዓቱም የማህበሩ አባላት፣ አርሶ አደሮች፣ የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከናውኗል።

የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳባ ሂርኮ፥ ማህበሩ በ12 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል መመስረቱንና ሕጋዊ ሰዉነት ማግኘቱን ተናግረዋል።

አክሲዮን ማህበሩ በ220 የሰበታ ሃዋስ ወረዳ: የሰበታ ከተማና የአካባቢዋ አርሶ አደሮች መመስረቱን የተናገሩት አቶ ዳባ ሂርኮ የማህበሩ ዋና አላማም የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነዉ ብለዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ሃይሉ በበኩላቸዉ በኢንቨስትመንት ምክንያት ከመኖሪያዉና ከመሬቱ ሲፈናቀል የነበረዉ የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን አርሶ አደር በቄዬዉ ላይ ወደ ኢንቨስትመንት መግባቱ ትልቅ ድል ነዉ ብለዋል።

ማህበሩ መመስረቱም የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለዉም ተናግረዋል።

በምስረታ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ፥ የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመረዉን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ለጃራ ሚልኪ የገበሬዎች አክሲዮን ማህበር መጠናከርም ተገቢዉን ድጋፍ እናደርጋለን ነው ያሉት።

አክሲዮን ማህበሩ በንግድ፣ በእርሻ፣በእሴት በመጨመር፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግንባታና በተለያዩ የአገልግሎት ስራዎች ላይ ተሠማርቶ እንደሚሰራ ኦቢኤን ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.