Fana: At a Speed of Life!

“ በምንም የማይተካ ህይወቱን ለሰጠ ጀግናው ሠራዊታችን የሚተካ ደም በመስጠታችን ደስተኞች ነን” – የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ደም ለግሰዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች “አገር ስትኖር ነው እኛ የምንኖረው፤ የአገር አንድነትን ለማስጠበቅ እየተዋደቀ ላለው የመከላከያ ሰራዊት ደም በመስጠታችን ደስተኞች ነን” በማለት ነው ደም የለገሱት።
በደም ልገሳው የተሳተፉት ተማሪዎች በምንም የማይተካ ህይወቱን ለሰጠ ጀግናው ሠራዊታችን የሚተካ ደም በመስጠታችን የላቀ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ደም ባንክ የሆሳዕና ቅርጫፍ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባሶሬ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ ደም እየለገሰ ይገኛል ብለዋል።
በደም ባንኩ ቅርንጫፍ ከህብረተሰቡ ደም እየተሰበሰበ መሆኑን አመልክተው፤ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተለይ የህልውና ዘመቻው በአሸባሪው ቡድኑ ላይ ከተጀመረ ወዲህ “ህብረተሰቡ በብዛት እየመጣ ደም እየለገሰ ይገኛል” ያሉት ሃላፊው፣ የህብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህል እጨመረ መምጣቱን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.