መከላከያ ሚኒስቴር ህብረተሰቡ ከሀሰት የፕሮፓጋንዳ መረጃዎች እንዲጠበቅ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሚኒስቴር ህብረተሰቡ በሀሰት ከሚሰራጩ የፕሮፓጋንዳ መረጃዎች ሊጠበቅ እንደሚገባ አስታወቀ።
የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያን ለማዳን እየተደረገ ያለው የህልውና ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል ።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሚነዛው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ህብረተሰቡ መረበሽ እንደሌለበት ተናግረዋል ።
አያይዘውም በሙጃና ድልብ አካባቢ ሰርገው የገቡ የሽብር ቡድኑ ሀይሎችን የመከላከል ስራም እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ ከትክክለኛ የመንግስት አካል ብቻ ምንጩን አረጋግጦ መረጃ መከታተል አለበትም ነው ያሉት ።
በተከዜ ወንዝ በጣለው በራሱ አስክሬን መንግስት ላይ የፕሮፓጋንዳ ጫና ለመፍጠር መሞከሩ ቡድኑ ያደገበት የማደናገር አካሄድ አካል ነው ብለዋል ።
በተኩስ አቁም ላይ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በመከላከል ወሳኝ ተልዕኮ ላይም እንደሚገኝም አስረድተዋል።
የሽብር ቡድኑ በምዕራብ ግንባርና በአፋር በኩል ሰብአዊና ቁሳዊ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበትም ነው የገለጹት ።
ህዝቡም ኢትዮጵያን ለማዳን እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።
በሀይለየሱስ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!