Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈጸመው ጥቃት ከ200 ሺህ በላይ ሺህ ዜጎች ተፈናቅለዋል- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

 

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈጸመው ጥቃት 200 ሺህ በላይ ሺህ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ አበይት ሣምንታዊ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብትና የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ክንውኖችን አንስተዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮችና የድንገተኛ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም በሰሜን ኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታዎች የተኩስ ማቆም እርምጃውን አሸባሪው ህወሓት ባለመቀበሉ የሠብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ መስተጓጎሉን አቶ ደመቀ አስታውሰዋቸዋል።

በአማራና በአፋር ክልሎች በተከፈተ ጥቃት ከ200 ሺህ በላይ ዜጎቸ ቢፈናቀሉም ኦቻን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አላወገዙትም በሚል ተገልጾላቸዋል።

ማርቲን ግርፍቲም ሠብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩና የመንግስትን ተኩስ አቁም እርምጃ ማድነቃቸውን አምባሳደር ዲና አንስተዋል።

በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሠላም ጓድ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ መሆኑን፤ ዓላማውም በሠብዓዊ ድጋፍና ገፅታ ግንባታ በመሳተፍ ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ጎን መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

በምጣኔ ሀብት ረገድ የኢትዮ-ናይጄሪያ የጋራ የንግድ ምክር ቤት ለመመስረት የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ከአናይጄሪያ አቻው ጋር መፈራረሙን፤ ይህም ለሁለትዮሽ ትስስር መጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁማል።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዘርፍ የዳያስፖራው ለሕዳሴ ግድብ ጠንካራ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ያወሱት ቃል አቀባዩ ለአብነትም በጁባ 80 ሺህ ዶላር፤ በአሜሪካም በቀን 124 ሺህ ዶላር መሰብሰቡን አስታውሰዋል።

አምባሳደር ዲና በሣምንቱ ከ500 በላይ ዜጎች ከምስራቅ አፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ የተለያዩ ሀገራት ከስደት ተመልሰዋልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.