የደቡብ ክልል ለመከላከያ ሠራዊት ሁለተኛ ዙር ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ህዝብና መንግስት ለመከላከያ ሠራዊት በሁለተኛ ዙር ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ የድጋፍ አሰባሰቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ ገለጹ።
በክልሉ ለሁለተኛ ዙር በዓይነትና በገንዘብ የተሰበሰበው የቁሳቁስና ገንዘብ ድጋፍ ወደ ግንባር መሸኘቱንም ተናግረዋል።
ከድጋፉ ውስጥ 40 ሚሊየን 243 ሺህ በላይ በጥሬ የተሰበሰበ ሲሆን 26 ሚሊየን 697 ሺህ በላይ የሚሆነው ገቢ በዓይነት በድምሩ 66 ሚሊየን 935 ሺህ ብር በላይ የሚገመት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
በዓይነት ከተሰበሰበው ገቢ 336 ሰንጋዎች፣ 55 በጎች፣ 279 ፍየሎች እንዲሁም ሌሎች ምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች መኖራቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የክልሉ ህዝብና መንግስት እስካሁን 104 ሚሊየን 167 ሺህ በላይ የሚገመት ድጋፍ በዓይነትና በገንዘብ ማድረጉን ወይዘሮ ፋጤ ገልጸው ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አውስተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!