በቤንች ሸኮ ዞን ህወሐትን የሚያወግዝና የሐገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አሸባሪው ህወሐትን የሚያወግዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
በሰልፉ ከስድስት ወረዳዎችና ከሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ትንሳኤ በተንኮልና በሴራ አይደናቀፍም፣ የህወሐት ጁንታ ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ጠላት ነው፣ በሉዓላዊነታችን ተደራድረን አናውቅም፣ በአንድነታችን ፊት የሚቆም ሀይል የለም የሚሉና ሌሎችም ህወሐትን የሚያወግዙ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍን የሚገልፁ መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
ከሰልፉ ጎን ለጎን በርካታ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ደም እየለገሱ ሲሆን ለሰራዊቱ የሚሆኑ የተለያዩ ስጦታዎች እየተበረከቱ ነው።
በተስፋዬ ምሬሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!