ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ተፋላሚ መሆናቸውን አረጋገጡ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊት ላይ በተካሄደው የቶኪዮ 2020 አትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ እንዲሁም የ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፈዋል፡፡
በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ለሜቻ ግርማ በ8 ደቂቃ 9 ሰከንድ ከ83 ማይክሮ ሰከንድ ሰዓት 1ኛ እንዲሁም ጌትነት ዋለ በ8 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ 2ኛ ሆኖ በመግባት ማጣሪያውን አልፈዋል፡፡
ሌላኛው ተሳታፊ ታደሰ ታከለ በ8 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ከ69 ማይክሮ ሰከንድ 9ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ ከፍጻሜው ውጭ ሆኗል፡፡
በሌላ በኩል በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ሀብታም አለሙ በ2 ደቂቃ 1 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ 2ኛ በመግባት ማጣሪያውን አልፋለች፡፡
አትሌት ነፃነት ደስታ በ2 ደቂቃ 1 ሰከንድ ከ98 ማይክሮ ሰከንድ ሰዓት 4ኛ ሆና በመግባቷ ከማጣሪያው ውጭ መሆኗን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!